የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴቢሶ አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት እንደገለፁት በአመቱ መጀመሪያ ተቋሙን ከዚህ ቀደም ከነበረው አካሄድ በተለየ መልኩ አዳዲስ ሪፎርሞችን በማምጣት በህግና በስነ-ምግባር መምራት ከተጀመረ በኋላ የሚታዩ ለውጦች መምጣትቱን ገለፁት ኮሚሽነሩ ተቋሙን በእውቀትና የሰው ሀይል በማደራጀት በተሰሩ በርካታ ስራዎች ጥሩ ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉንም አመልክተዋል።
ከህብረተሰቡ አመኔታን ለማግኘት ከተሰሩ ስራዎች በበተጨማሪ የህብረተሰቡን እርካታ ለመጨመርና በየእርከኑ የተሰሩ የወንጀል መከላከል ተግባራት በማጠናከር ሌሎች ክፍተቶች ላይ በትኩረት በመስራት የ2019 እቅድን ለማሳካት ሁሉም የተቋሙ አመራርና አባላት ሀላፊነቱን በተገቢው መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል ።
በወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ስራ 12% መቀነስ መቻሉንና በምርመራ ዘርፍ ካምናው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር አበረታች ውጤት ተመዝግቧል በሙስና ወንጀሎች 120 ክሶች ለዐቃቤ ህግ የተላለፈ ሲሆን በሙስና የተመዘበረ 7216,591.15 ብር ለመንግስት ገቢ ማድረግ ተችሏል።
በሰው ልጆች ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እያስከተለ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል በተከናወነው ስራ ከተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 25% አደጋ መቀነስ የተቻለ ሲሆን ደንብ ተላልፈው በተገኙ 66,347 አሽከርካሪዎች ተከሰው 64,497,754 ( ስልሳ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ አራት ብር) ለመንግስት ገቢ ሆኗል።
የአባላትን አቅምን ለማሳደግ በረዥምና አጫጭር ጊዜያት ስልጠናዎችን በመስጠት አቅም በመገንባት ብቃት ያለው የፖሊስ ሀይልን የመፍጠር ስራ የተሰራ ስሆን ኃላፊነታቸውን በተገቢው ባልተወጡና የስነ-ምግባር ችግር በታየባቸው 25 የትራፊክ ፖሊስ አባላትን በደሞዝና ከሙያቸው በማንሳት እርምጃ ተወስዷል።
ከወንጀል መከላከል ስራ ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት ለ40 አቅመ ደካማ ቤተሰብ ቤቶችን በመገንባትና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡና እርዳታ ለሚሹ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በመጨረሻም አመራሮቹ በቀረበው ሪፖርት መነሻ በሰጡት በአስተያየት በሁሉም ዘርፎች ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በድክመት የተለዩትን በማረም በስኬት የተከናወኑትን ለማስቀጠል በየጊዜው አፈፃፀምን መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
መድረኩ የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም የ2019 በጀት አመት እቅድን በማፅደቅ ተጠናቋል።



