🚨 ነፃ የስልክ ጥሪ:- የሲዳማ ክልል: 8295 | የሀዋሳ ከተማ: 7614 | የፈደራል: 991
ሲዳማ ፖሊስ | SIDAMA POLICE

ጠቅላይ መምሪያ ጽ/ቤት የመገናኛ አማራጮች

Head Quarter Office Contact Information


በጠቅላይ መምሪያ ጽ/ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች
  • ህገ መንግስትንና ህገ መንግስቱን ተከትሎ የሚወጡ ህጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን አክብሮ የማስከበር ስራ ይሰራል፤
  • የመምሪያውን ስራዎችን ያቅዳል ፤ያደራጃል ፤ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤
  • የተቋሙን ስትራቴጂ እቅድ ተከትሎ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ በሚሰጡት አቅጣጫ መሰረት የስራ ክፍሎችን ዓመታዊ እቅድ ረቂቅ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ የተዘጋጀው እቅድ በጠቅላይ መምሪያው ኃላፊ በማስተቸት ያስፀድቃል፤ የፀደቀውን እቅድ ለሚመለከተው ያሰራጫል፣ አፈፃፀሙን ክትትል ያደርጋል፤
  • አጭር ዕቅድ ወጥቶላቸው ሊተገበሩ የሚገባቸው ስራዎች ሲኖሩ እቅድ በማውጣት ለጠቅላይ መምሪያው ኃላፊ ያቀርባል፤
  • ለመምሪያው ተጠሪ ከሆኑ ስራ ክፍሎች የሚላኩ ዕቅዶችን በመገምገም የሚጎድላቸውን ጉዳይ በመለየት እንዲስተካከሉ ምክረ ኃሳብ ለጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ በማቅረብ ግብረ-መልስ ይልካል፤ ይከታተላል፤
  • ለጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ሊቀርቡ የሚገባቸውን ሪፖርቶች፣ መግለጫዎች፣ ዘገባዎችና ማስታወሻዎችን በአግባቡ በማጣራት አስፈላጊ ከሆነም በአጭርና ግልጽ በሆነ መልኩ በመፃፍ ለውሳኔ አመቻችቶ ያቀርባል፤
  • ከመምሪያው ወደ ሚመለከታቸው ክፍሎች የሚላኩትን መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች በወቅቱ በማዘጋጀት ለጠቅላይ መምሪያው ኃላፊ ያቀርባል፤ ይከታተላል፣
  • ከጠቅላይ መምሪያዉ ኃላፊ ጋር በመሆን በስራ ክፍሎች እቅድና ሪፖርት ዝግጅት የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን እና የአቅም ውስንነቶች በመለየት በአስተዳደርና ልማት ስልጠና የሚሰጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • ከጠቅላይ መምሪያው ኃላፊ የሚሰጡ የስራ ተግባራትን በመምሪያው ስር ለሚገኙ የስራ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ተግባራዊ ስለመሆኑም ክትትል ያደርጋል፣ ስለአፈጻጸሙም ለጠቅላይ መምሪያው ኃላፊ ሪፖርት ያቀርባል፤
  • የልዩ ልዩ የስብሰባ ጥሪዎችንና አጀንዳዎችን ለሚመለከታቸው በወቅቱ ያስተላፋል
የጠ/መምሪያ ጽ/ቤት አባላት

የጠ/መምሪያ ስም ጠቅላይ መምሪያ ጽ/ቤት
የአባላት ብዛት (ወንድ)
የአባላት ብዛት (ሴት)
አጠቃላይ አባላት ብዛት

ጠ/መምሪያ መዋቅር 


ጠቅላይ መምሪያ ጽ/ቤት መዋቅር | Crime Prevention Structure