የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ⭐
📜 ታሪካዊ ዳራ — የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ
የዘመናዊ ፖሊስ አጀማመር በኢትዮጵያ
በሀገራችን ዘመናዊ የፖሊስ ተቋምን የማደራጀትና አገልግሎቱን የማስተዋወቅ ተግባር ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መሆኑን የተለያዩ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ፖሊስ በተቋም ደረጃ በአዋጅ የተቋቋመው ከጥር 23 ቀን 1934 ዓ.ም (1942 እ.ኤ.አ) ጀምሮ ነው፡፡
በተለያየ ጊዜ የአራዳ ዘበኛ፣ የከተማ ዘበኛ፣ ዋርድያ በሚል የተለያየ አጠራር የተጀመረው የሀገራችን የፖሊስ አደረጃጀት እስከ 1948 ዓ.ም ድረስ የፓራ ሚሊቴሪ ቅርጽ የነበረው ሲሆን በከተማ ወቅቱ የፈቀደለትን ቴክኖሎጅ በመኪና፣ በሞተርና በብስክሌት እንዲሁም በገጠር ደግሞ በፈረስ፣ በበቅሎና በግመል እየታገዘ የፖሊስን ስራ ለማከናወን የተቻለበት ዘመን እንደነበረ ከታሪክ እንረዳለን፡፡
🏛️ የሲዳማ ፖሊስ ምስረታና እድገት
የሲዳማ ፖሊስ የደርግ አገዛዝ ውድቀት ተከትሎ ሰኔ 14/1984 ጀምሮ በሽግግር መንግስት ስር አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ታሪክ ይነግራል። በ1987 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ር ሕገ መንግሥት መጽደቁን ተከትሎ በተወቀሩ ክልሎች ውስጥ የቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት አወቃቀር ውስጥ በነበሩ የዞን መዋዕቅሮች ውስጥ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በህግ፟መንግስቱ መሰረት ተቋቁሟል።
በዚህ መዋዕቅር ውስጥ በሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ስያሜ ይዞ በየደረጃው ከሚገኙት ከፀጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት የሕዝቦች ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሚና በአግባቡ ሲወጣ ቆይቷል፡፡
📌 ቁልፍ ክንውን፡- የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በለውጡ መንግሥት አወንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውን ተከትሎ በሕዳር 10/2012 ዓ.ም በተደረገ ሕዝበ ውሳኔ 10ኛ ክልል ሆኖ መደራጀቱን ተከትሎ ከዞን መዋዕቅር በወቅቱ የነበረው ስያሜ በመቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 7/2012 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሚል ስያሜ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡
📅 ዋና ዋና የታሪክ ገፅታ (ጊዜ መስመር)
1934 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዘመናዊ ፖሊስ መቋቋም
1987 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ር ሕገ መንግሥት መጽደቅ
2012 ዓ.ም ሲዳማ 10ኛ ክልል መሆን
2017 ዓ.ም የሲዳማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መቋቋም
ቀጣይ ዘመናዊ ማሻሻያዎች
👥 የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች (2012-2018 ዓ.ም)
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 10ኛ ክልል ሆኖ ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አመታት በኮሚሽነርነት የክልሉ ፖሊስ ተቋም የመሩ አመራሮች።

(ሐምሌ 2012 - ታኅሣሥ 2013 ዓ.ም)

(ታኅሣሥ 2013 - መስከረም 2014 ዓ.ም)

(መስከረም 2014 - ጥር 2015 ዓ.ም)

(መጋቢት 2015 - ሰኔ 2018 ዓ.ም)
ተፅዕኖ እና ተስፋ
ምንም እንኳን አዲስ መዋቅር ቢሆንም፣ የሲዳማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በተሻሻለ አስተዳደር፣ ቁጥጥር እና የተቋማት ማሻሻያ በሲዳማ ኢኮኖሚ ማጠናከር ዋና ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ወደፊትም የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ዘመናዊ የፖሊስ አገልግሎት ለማዳረስ ቁርጠኛ ነው።
🎯 ዓላማ እና ዋና ተግባሮች
የቁጥጥር እይታ
የክልሉ የሕዝብ ተቋማትን አፈፃፀም፣ አስተዳደር እና የፋይናንስ ታማኝነት መከታተል።
የሕዝብ ፍላጎት ጥበቃ
ግልጽነት፣ ታማኝነት እና ከማህበራዊ–ኢኮኖሚ ግቦች ጋር ተያይዞ እንዲሠሩ ማረጋገጥ።
የአፈፃፀም ማሻሻያ
ውጤታማነት፣ ተደራሽነት እና የአገልግሎት ጥራት ማበረታታት።
የማሻሻያ እንቅስቃሴ
በክልሉ የልማት ቅድመ ተልዕኮ የሚጣጣሙ የድርጅት ማሻሻያዎችን መምራት እና መደገፍ።
🗺️ ሲዳማ ክልል - ጂኦግራፊያዊ ገጽታ ከባህር ወለል በላይ 1,500-3,000ሜ
ስለ ሲዳማ ክልል
ሲዳማ ክልል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን በሕዳር 10/2012 ዓ.ም (ኖቬምበር 20, 2019 እ.ኤ.አ) በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ መሠረት የኢትዮጵያ 10ኛ ክልል ሆኖ ተቋቋመ። ክልሉ በሀገሪቱ ከሚገኙ ልዩ የአየር ንብረት እና የተፈጥሮ ሀብት ባለፀጋ አካባቢዎች አንዱ ነው።
ከላይ በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው የሲዳማ ክልል በአራት ዋና ዋና የአግሮኢኮሎጂካል ዞኖች የተከፋፈለ ነው። እነዚህም፦ ቆላ፣ ወይና ደጋ፣ ደጋ እና ዉርጭ ይባላሉ። ይህ ክፍፍል ከባህር ወለል በላይ ባለው ከፍታ፣ በአየር ንብረት እና በእርሻ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ ነው።
ክልሉ በቡና፣ በእንሰት፣ በበቆሎ፣ በገብስ፣ በስንዴና በሌሎች የእህል ዓይነቶች የታወቀ ነው። በተለይም የሲዳማ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ በልዩ ጣዕም የሚታወቅ ነው።
የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ ሲሆን በበርካታ የቱሪስት መስህቦች የበለፀገ ነው።



