የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ "ፍቼ ጨምበላላ" በዓል በሰላም ተከብሮ እንድጠናቀቅ በተዘጋጀው  የፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።

የበዓሉ አከባበር አስመልክቶ በተዘጋጀው የፀጥታ ዕቅድ በክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በረዳት ኮሚሽነር ፍቅሬ ዮኢሳ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

‎በክልሉ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የፍቼ ጨምበላላ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንድጠናቀቅ ከፀጥታ ግብረሃይል ፣ ከህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች እና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

‎የውይይቱ ተሳታፍዎች በቀረበው የፀጥታ ዕቅድ መሠረት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንድጠናቀቅ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመፈፀም ወትሮ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

‎በውይይት መድረኩ የክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፍት አመራሮች፣ብሔራዊ ደህንነት ፣የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና የዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነት ስባል በፀጥታ ግብረ ኃይል የሚተላለፉ ውሳኔዎች በቀጣይ ለህዝብ የሚገለፁ መሆናቸው በፀጥታ ዕቅዱ ተመላክቷል።

‎ፍቼ ጨምበላላ በዓል መጋቢት 5 እና 6 2018 ዓ/ም ይከበራል።

ለተጨማሪ ፖሊሳዊ መረጃዎች

https://www.facebook.com/share/1ArLo6BLbC/

‎Telegram:- https://t.me/SIDAMAPOLICE

https://whatsapp.com/channel/0029VbBbBn9GpLHXYN9gJ537

tiktok.com/@sidamapolice4656

https://www.youtube.com/@Sidamapoliceheadquarter