የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ተስፋዬ ደቢሶ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ የተመራውን ልዑክ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ። ክቡር ጀነራል ነብዩ ዳኜ በክልሉ ፖሊስ እየተሰሩ የሚገኙ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና ተቋማዊ አሰራሮችን ምልከታ አድርገዋል።
ተቋሙ የጀመራቸውን የቴክኖሎጂ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ክቡር ጀነራል ነብዩ ዳኜ አመላክተው ተቋሙ ለሰራተኛው ምቹ ቦታን ከመፍጠር አኳያና ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለበት ሂደት አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሰው ሀይልን ለማብቃት በሚሰራው ስራ የፌዴራል ፖሊስ ከጎናቸው መሆኑን ገልፀዋል።



