የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አድሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ ማዕከል በህክምና ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የጉብኝትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ።
በዕለቱ የድጋፍ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴብሶ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የኩላሊት እጥበት ህክምና ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ባለን አቅም መደገፍ፣ ማበረታታትና አለኝታነታችንን ማሳየት የህሊና እርካታ የሚሰጥና የወገን ደራሽነትን እሴት የሚያጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስቀድሞ ዕቅድ በማዉጣት ፣የህብረተሰብ አለኝታነቱን ለማረጋገጥ በተለያዬ ችግር ዉስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን "ለወገን ደራሽ ወገን" በመሆኑ ካለዉ በማካፈል ለበርካታ ወገኖች ልዩ ልዩ ድጋፍ እያደረገ የቆዬ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነር ተስፋዬ ዴብሶ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል በኩላሊት እጥበት ህክምና ላይ እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወገኖቻችን የጠቅላይ መምሪያዉ አመራርና አባላት ካላቸዉ የደመወዝ ገቢ በመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ይህ ድጋፍ በዚህ የሚያበቃ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው መሆኑን አስታውቋል ።
የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸዉ የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይህን በጎ ተግባር በማሰብ ላደረጉት ነገር አድናቆታቸዉን ገልፀዉ ይህ ድጋፍና ጉብኝት የማዕከሉን ተስፋ የሚያጎለብት ከመሆኑም ባሻገር ፣ የሀገርና የትውልድ ባለውለታ የሆኑ አባቶቻችን እና እናቶቻችን አስፈላጊዉን ህክምና እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑን አብራርተው ይህንን ድጋፍ ያበረከቱ ቅን ልቦች በእጅጉ ልመሰገኑ ይገባል በማለት ፖሊስ አርዓያነቱን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል ።
በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል !



